Skip to main content

Posts

Showing posts from November, 2019

የድር አካውት ጥበቃና ጥንቃቄ (Web account Security and Safety)

የድረገፅ ትግበራዎች (web applications) ባለንበት ዘመን የኑሯችን አካል ሆነዋል ። ከኢሜል ጀምሮ እስከ ባንክ አካውንት ለስራም ሆነ ለመዝናኛ ብዙ የኦንላይን አካውንቶችን እንጠቀማለን። እነዚህ አካውንቶች የያዙትን የግል ውህብ (private data) ለመጠበቅና የውህቡ ባለቤት ብቻ የመጠቀም መብት እንዲያገኝ የሚያስችለው የአካውንቱ ባለቤት በሚስጥር የሚይዘው የይለፍ-ቃል(password) ነው ። ታዲያ ካሉት የኦንላይን አካውንቶች ብዛት አንፃር አንድ ሰው ስንት የተለያዩ የይለፍ-ቃሎች ይኖሩታል ? የኦንላይን አካውንቶች ብዛት እየጨመረ ሲሄድ የይለፍ-ቃሎችን በተደጋጋሚ ወይም ትንሽ ለውጥ በማድረግ ደጋግሞ መጠቀም የብዙ ሰዎች ባህሪ ነው ። ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ማካፊ በሰሜን አሜሪካ በሰራው ጥናት ከ 30% በላይ የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች የይለፍ-ቃሎችን ደጋግመው እንደሚጠቀሙ ነው የጠቆሙት።